Bedessaን በስልካቸን

Bedessaን በስልካቸን Visit bedesa

በተደደጋሚ አሰከፊ የትራፊክ አደጋ ለሚከሰትበት ለበዴሳ ከተማ አከባቢ ዘላቂና ፍቱን መፍትሔ ለከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች የሚሆን   (Bypass highway) መገንባት ያስፈልጋል።=======...
11/04/2026

በተደደጋሚ አሰከፊ የትራፊክ አደጋ ለሚከሰትበት ለበዴሳ ከተማ አከባቢ ዘላቂና ፍቱን መፍትሔ ለከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች የሚሆን (Bypass highway) መገንባት ያስፈልጋል።
==========================

በበዴሳ ከተማ ውስጥ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሐዋሳ በሚዘልቀው የአገር አቋራጭ መንገድ ከማዮ ቆቴ እስከ በዴሳ ወንዝ ድረስ ወደ 15 ኪሎ ሜትር የሚሆነው ከፍተኛ ቁልቁለት በመሆኑ እና የአስፋልት መንገዱ ሲሠራ የመንገድ ደህንነት እርምጃዎች አስቀድሞ በሳይንሳዊ ጥናት መሠረት ባለመወሰዱ በተደጋጋሚ የሰው ሕይወት እየቀጠፈ፣ ከፍተኛ የንብረት መውደም እያስከተለ እና ዜጎችን ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና እያዳረገ ይገኛል።

ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሻሸመኔ ዲስትሪክት የተወሰኑ የመፍትሔ እርምጃዎችን ለአብነት፦ የፍጥነት መቀነሻ/speed break) በተወሰኑ አከባቢዎች መሥራቱ፣ የማስጠንቀቂያ ቢልቦርድ ብሰቅልም፣ የመንገድ ዳር ምልክት ብተክልም እንዲሁም የመንገድ ጎን መከላከያ ኮንክርት ግንብ በበዴሳ ወንዝ አከባቢ ቢገነባም ችግሩን በዘላቂነት መፍታት አልቻለም፤ በወቅቱ የተጀመሩ መልካም ሥራዎቹም ሳይጠናቀቁ መንገድ ላይ ቆሟል። ከማዮ ቆቴ ቀበሌ ዳልቦ ማዞሪያ እስከ በዴሳ ወንዝ ድረስ አሁንም የመንገድ ደህንነት ሥራዎች በልዩ ትኩረት ቢሠሩ መልካም ነው።

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ፍቱን አማራጭ መፍትሔ ከባባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የትራፍክ መጨናነቅ ያለበትን የከተማውን መሐል መንገድ ትቶ የከተማውን ዳር አቋርጠው የሚያልፉበት 4 ኪሎ ሜትር የሚሆን የማሳለጫ መንገድ መገንባት ነው። አሁን ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፈው መንገድ ዲዛይን ቁልቁለታማ ቦታዎችን የሚቀንስና በባለወልድ ቤተክርስቲያን በራፍ አድርጎ የሚያልፈው የትራፊክ አደጋን የሚቀንስ ከመሆኑም በተጨማሪ የከተማዋን ዕድገት የሚያሳልጥ ነበር፤ አሁን ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፈውም ቢሆን በአማራጭነት የሚሠራበት ዕድሎች የነበሩ ቢሆንም ምክንያታዊ ባልሆነ በእርስ በርስ ጭቅጭቅ የመከነ ዕድል ሆኗል።

ወደ በዴሳ ከተማ ከመገባቱ አስቀድሞ በቢልቦ በዴሳ፣ በባለወልድ ቤተክርስቲያን ዞሮ እስከ በዴሳ ወንዝ የሚዘልቅ ማሳለጫ መንገድ ቢገነባ በከተማው ውስጥ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ፣ የትራፊክ አደጋን በመቀነስ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትን በማሳለጥ፣ የትራፊክና የመንገድ ደህንነትን በማሻሻል፣ የከተማውን ገጽታ በማሻሻል፣ ወዘተ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን ከማስገኘት አንጻር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። [ከሙያዬ አንጻር የሰጠሁት የግል አስተያየቴ እንደሆነ ልብ በሉልኝ]

በመሆኑም የፈዴራል መንገዶች ባለሥን ERA ለዚህ መንገድ በመፍትሔ ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል፡፡
ዘውትር የዜጎቻችን ሕይወት መገበር እና የልብ ስብራት በቃ ልባል ይገባል።

30/10/2025
የበዴሳ ከተማን ከብዙ በጥቂቱ እናስተዋውቃችሁ :-************የምስራቅ ንጋት ፣ ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ የሆነችው የበዴሳ ከተማ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲና ወላይታ ሶዶ...
06/04/2025

የበዴሳ ከተማን ከብዙ በጥቂቱ እናስተዋውቃችሁ :-
************
የምስራቅ ንጋት ፣ ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ የሆነችው የበዴሳ ከተማ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲና ወላይታ ሶዶ በ24 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች ።

ከተማዋ መንፈስን በሚያድስ ከብልቦ በዴሳ ፍል ውኃ ምንጭ በሚመነጭ ንጺህ የመጠጥ ውኃ የታደለች፣ ተስማሚ የአየር ፀባይ ያላት፣ ጥራት ያለውን የግንባታ ግብዓቶችን አሸዋ፣ ድንጋይ፣ ጠጠር፣ ፑሚስ፣ ጋራጋንቲ/ቀይ ዐፈር /፣ ሴሌክትድ ማቴሪያል፣ ባህር ዛፍ እና ጣውላ በውስጧ አቅፋ የያዘች በመሆኗ ለኢንቨስትመንትና ለንግድ ተመራጭ ያደርጋታል።

በብዙ የውጭና የሀገር ቱሪስቶች የሚጎበኝና በቱሪስት መዳረሻነት የታወቀውን የባንበላ ሰው ሰራሽ ተንጠልጣይ ድልድይ፣ የበዴሳ ኒውዮርክ ተብሎ የሚጠራው የባንበላ ሥነምህዳር፣ በፈዋሽነቱ ወደር ያልተገኘለት የብልቦ ፍልውኃ፣ እና ሌሎች የቱሪስት መስህቦች ያላት ናት በዴሳ ከተማ ።

እንግዳን በፍቅር ተቀብሎ በፍቅር የሚያስተናግድ፣ በአብሮነት፣ በአንድነትና በፍቅር ተቻችሎና ተከባብሮ የሚኖር ሕዝብ ያላት ከተማ ናት ።

# ኑ በበዴሳ ከተማ :-
@ ይኑሩ
@ ይነግዱ
@ ኢንቨስት ያድርጉ፤ በእርግጠኝነት ትርፋማ ይሆናሉ ።

መጋቢት 28/2017 ዓ/ም

ይቀጥላል .....

ምስጋና ለበዴሳ ከተማ ነዋሪዎች እና የፖሊስ አባላት በሙሉ   #አደጋው ሲደርስ ተረባርበው ወደ  #ህክምና ለወሰዱ የአከባቢው ነዋሪዎች ክብር ምስገና ይገባቹሀል አስክሬን ለይተው ንብረት በዓይ...
24/03/2025

ምስጋና ለበዴሳ ከተማ ነዋሪዎች እና የፖሊስ አባላት በሙሉ

#አደጋው ሲደርስ ተረባርበው ወደ #ህክምና ለወሰዱ የአከባቢው
ነዋሪዎች ክብር ምስገና ይገባቹሀል አስክሬን ለይተው ንብረት
በዓይነት ለይተው ለፖሊስ በማስረከብ የአከባቢው ወጣት
#ከፖሊስጋ ሂኸት ለማዳን ያደረጉት ጥምረት ቦታው ድረስ ሄጄ ያገኘሁዋቸው ያለውን ሁኔታ አካፍለውኛል ።

እንዲህ አይነት ማህበረሰብ በሀገራችን ያብዛልን ሰብአዊነት ታማኝነታቸው ፅናታቸው እጅግ በጣም ጠንካሮች
ውለታችሁን ፈጣሪ ይክፈላችሁ ። shashemane

  ሰላም እንደምን ቆያችሁ የሀገረ ልጆች ዛሬ አንድ መልካም ዜና ይዤላችሁ መጥችያልሁ ፥ እሱም ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ትልቅ ዕድል ከፊት ለፊት መጥቷል ፤ ይሄ ዕድል ለእኔ ከምንም በላይ ደ...
13/03/2025


ሰላም እንደምን ቆያችሁ የሀገረ ልጆች ዛሬ አንድ መልካም ዜና ይዤላችሁ መጥችያልሁ ፥ እሱም ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ትልቅ ዕድል ከፊት ለፊት መጥቷል ፤ ይሄ ዕድል ለእኔ ከምንም በላይ ደግሞ ስለ እኔ ስኬትና በትልቅ ደረጃ መገኘትን ስትመኙልኝ ለነበራችሁ ለእናንቴ ደግና ሁሌም ከጎኔ ለማትጠፉ ከምንም ጊዜውም በላይ ታላቅ ደሰታ የሚፈጥር አጋጣሚ ነው ።

ወደ ዝርዝር ጉዳዩ ስመለስ እግዚአብሔር ረድቶኝ በሀገረችን ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላላቅ አትሌቶችን በማፍራት የሚታወቀው ለአብነትም እኔ የአትሌት ሂሩት መሸሻ ፣ ጽጌ ዱጉማ እና ሌሎችም ታላላቅ አትሌቶች አሰልጣኝ የሆነው Alemu Wakjira ወደሚያሰልጥነው 'Global Middle Distance Athletics Team In Ethiopia' ስለተቀላቀልኩኝ በቡድኑም ውስጥ ለአንድ ዓመት ገደማ በአሰልጣኝ ዓለሙ ዋቅጅራ ሥር እየሰራው ለማሳለፍ ከስምምነት የደረስኩ ስሆን በማሳልፋቸው
1 ዓመት ውስጥ የተለያዩ የውጭ የውድድር ዕድሎችን ማግኘት እንደምችልና ከዝያም በኃላ ራሴን ችዬ በተለያዩ ውድድሮች አሸናፊ መሆን እንደምችል በመተማመን ነግረውኛል ።

ለዚህም ቆይታዬ Global Middle Distance 80% ወጪውን ሸፍኖልኝ ቀሪውን 20% ወጭውን ማለትም የአንድ ዓመት የቤትና የቀለብ ውጪያዬን እንድሸፍን ነግረዉኛል ፣ እኔም እናንተን የሁል ጊዜም አለኝታዎቼን የሀገረን ልጆች ተማምኜ እሽ ብዬ ተመልሽያለሁና በተቻላችሁ መጠን ህልሜ እዉን እንድሆን ከጎነ እንድትቆሙ አደራ እላችኋለሁ !!

ከዚህ በፊትም ፣ አሁንም እየደገፈችኝ ስፖርት ትጥቅ ከአየርላንድ እያመጣች አይዞህ ፣ በርታ በማለት እዚህ ደረጃ እንድደርስ ላደረገችኝ Bereket Adera ትልቅ ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁ !! እግዚአብሔር ያክብርልኝ !! የወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ፣ እግዚአብሔር በገንዘብ የባረካቸዉ ባለሀብቶች ፣ መላዉ ልቤ ቀና ኢትዮጵያዊያን ከጎነ እንድትቆሙ ጥሪያዬን አቀርባለሁ !! Via: Meki Mekonen 🤝

: 1000243401864
Meklit Mekonin Jaldo

#ስልክ: 0940018358

በዳሞት ወይዴ ወረዳ ከ7 ሚልዮን ብር በላይ ለሚገነባው ድልድይ የመሠረተ ድንጋይ ተጣለዳሞት ወይዴ፤ መጋቢት 4/2017 ዓ/ምበዳሞት ወይዴ ወረዳ ከ7 ሚልዮን ብር በላይ በBMW Mission እ...
13/03/2025

በዳሞት ወይዴ ወረዳ ከ7 ሚልዮን ብር በላይ ለሚገነባው ድልድይ የመሠረተ ድንጋይ ተጣለ

ዳሞት ወይዴ፤ መጋቢት 4/2017 ዓ/ምበዳሞት ወይዴ ወረዳ ከ7 ሚልዮን ብር በላይ በBMW Mission እና በ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በጋራ ለሚገነቡት
በበዴሳ ወንዝ ላይ የብልቦ በዴሳ፣ የበዴሳ ከተማ፣ የቶራ ኦፎሬ፣ የኮዮ ሳኬ እና የሙንዳጃ ሳኬ ሕዝብን የሚያገናኝ ድልድይ ግንባታ የመሠረት ድንጋይን በዛሬው ዕለት አስቀምጧል ።

የድልድይ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ በሚጣልበት ቦታ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክሌ ቶማ እንደገለጹት ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ አንዱ ለሌላው የደም መስዋዕትነት የከፈሉ ህዝቦች መሆናቸውን በማስታወስ በBMW Mission እና በ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በጋራ በበዴሳ ወንዝ ላይ ለሚገነቡት የሣኬ እና በዴሳ የሕዝብ መገናኛ ድልድይ የመሠረት ድንጋይ በመጣላቸው በወረዳው መንግስት ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ።

በBMW Mission እና በ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በጋራ በዳሞት ወይዴ ወረዳ ከዚህ ቀደም በበዴሳ ከተማ ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ኮዮ ሣኬ እና ቶራ ኦፎሬ ቀበሌያትን የሚያገናኝ ድልድይ እንዲሁም አሁን በበዴሳ ወንዝ ላይ የሣኬ ክላስተር እና የበዴሳ ሕዝብን የሚያስተሳስር መገናኛ ድልድይ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ በመጣሉ በድጋሚ አቶ ተክሌ አመስግነዋል ።

መንገድ ለሁሉም ነገር መሠረትና የደም ስር መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተክሌ አሁን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት ቦታ የሰው እና የቤት እንስሳት ህይወት የቀጠፈ በመሆኑ የአከባቢው ህብረተሰብ ይህን ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ድልድዩ ስገነባ በገንዘብ፣ በዕውቀት እና በጉልበት እንዲያግዙ አሳስበዋል ።

ድልድዩ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የወረዳው መንግስት ከድልድዩ ወደ በዴሳና ወደ ሣኬ መንገድ ድረስ የመንገድ ሥራ እንደሚሰራ አረጋግጧል ።

የ South Korea BMW President PR CHUN በበኩላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ በኮሪያ ጦርነት ለከፈለው የሕይወትና ደም መስዋዕትነት የኮሪያ መንግስት ሁሌም እያሰታወሰ መኖሩን በመጠቆም የኮሪያ መንግስት በምላሹ ደም ለመስጠት ምስክርነቱ በወረዳው ትምህርት ቤት መገንባቱ፣ የሣኬና የቶራ ኦፎር ቀበሌ የሚያገናኝ ድልድይ ገንብቶ ማሰረከቡ እና አሁን በተጨማሪ በዴሳ ወንዝ ላይ የሣኬ እና በዴሳ የሕዝብ መገናኛ ድልድይ ለመገንባት
የመሠረት ድንጋይ መጣሉና ወደ ሥራ መግባቱ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል ።

ፕሮጀክቱ ወደ አከባቢያችን እንደመጣና ወደ ሥራ እንዲገባ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ፓስተር ዳዊት ጉድኖ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፕሬዚደንት እና አቶ ዮሰፍ ቶጋ የቀድሞ በደቡብ ኮሪያ የደቡብ ኢትዮጵያ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አስተባባሪ የሆኑትን በወረዳው ሕዝብ ስም ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል አቶ ተክሌ።

በመጨረሻም የበዴሳ የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሥራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል ።

የመሠረተ ድንጋይ በሚጣልበት ቦታ ላይ የወረዳው ፊት አመራሮች፣ በBMW Mission President እና አባላት እንዲሁም የአከባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል ። Tekle Toma 👏👏

ከዝህ ቀደም በዳሞት ወይዴ ወረዳ ያሉ ለውጥ ፈላጊ እናም በአብሮነት መስራት የሚፈልጉ መልካም ሰዎችን ብናስተባብር መበራት ማስገባት ከባድ እንዳልሆን በጥቂቱ ለማስቀመጥ ሞክሬ ብዞች ሼር ስታደ...
10/03/2025

ከዝህ ቀደም በዳሞት ወይዴ ወረዳ ያሉ ለውጥ ፈላጊ እናም በአብሮነት መስራት የሚፈልጉ መልካም ሰዎችን ብናስተባብር መበራት ማስገባት ከባድ እንዳልሆን በጥቂቱ ለማስቀመጥ ሞክሬ ብዞች ሼር ስታደርጉና ሀሳብ ስሰጡ እንደነበረ የሚታወስ ነው። ይህን ሀሳብ አሁን ላይ ያሉ ህዝብንና ወረዳውን የሚያሰተዳድሩ ሰዎች ያካህዱታል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።
እንደወትሮየ ዛሬም አንድ ሀሳብ ሰለ ዳሞት ወይዴ ባስቀምጥ ቢዬ አሰብኩ። ሁላችንም የዳሞት ወይዴ ለውጥን ከሚጋባ በላይ እንደምንናፍቅ አምናለው። ለዛም ነው በሰው ዘንድ ያሉ ሀሳቦች ቢወሰዱ እናም መልካም መስለው ከታዩ ህበረተሰብን ባማከለ መንገድ በአብሮነት ለውጥ ማምጣት ብዙም እሩቅ ጊዜ አይወስድም።
ዛሬ ከውድ ጓደኞቼ ጋር እየተራመድኩኝ የዋናው መንገድ ውበት ከዝህ ቀደም ከነበረበት እየቀነሰ ይገኛል.....
1,በመንገድ መሃል ያለው በወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ እርዳታ ችግኝ በማገኘትና በበዴሣ ሰባተኛ ቀን አክባሪ አድቨንቲስት ችገኝ የሚተከለበትን ጉድጓድ በመቆፈር እንድሁም በዳሞት ዎይደ ማዘጋጃና 02 ቀበሌ እርዳታ ጽዱ እና ውብ ለማድረግ ተለፍቶበት እንደነበረ የሚታመን ነው። ነገር ግን የተተከለው ችግኝ በውሃ እጥረትና በጥበቃ ማነስ ከግማሽ በላይ ችግኞች መሞት ችለዋል። አሁን ላይ የከተማውን ውበት ለችግኝ ተብሎ የታጠረው የእንጨት አጥር ወበቷን አሳጥቷታል።
👉ስለዝህም የእንጨት አጥር ሙሉ ቢነሳ እና በከተማ ውስጥ ያሉ 01 ቀበሌ እና 02 ውስጥ ያሉ ለውጥ ናፋቅ ማህበረሰብ አንድ ላይ በመሆን ቢኮተኩቱ፣
👉እንዲሁም ማዘጋጃ እና ከተማ ልማት በአንድነት ችግኝ የሚገኝበትን መነገድ ቢፈልጉ፣እንድሁም ጥበቃና የከተማ ፅዳት ቢቀጥሩ እናም ከበድ ያለ ህግ ቢያወጡ ችገኝ ውስጥ ለሚገቡ ሰውና ከብት ላይ፤
👉በውሃ የማትታማ ወረዳ በዞን ውስጥ በዴሳ ናትና ውሃ ልማቶች በችግኝ መሃል በየሁለት መትር ቧምቧ ቢገጥሙ፤ በራሳችን ያለማንም እርዳታ የተሻለ ወብ እና ለምለም ማድረግ ይቻላል።
2)))) በ 02 ቀበሌ ዋና መንገድ ዳር ያለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰፊ ቦታ መውሰዱ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ያለን የወረዳችን ስፋት ጥቂትም ሰለሆነ መንገድ ዳርም ውበት ልኖረው ስለሚገባ፣ከፊት ያለውን ቦታ ለእንቨትመንት ቢጠቀሙ፣ አልያም ለንግድ ምቹ ሰለሚሆን በሊዝ ለነጋድዎች ቢሰጥ እና የትምህር ቤት መገቢያ እና የልጆች መቦረቅያ በወትሮ ሳር ሰፈር በሚባልበት መንደር ቢደረግ ቦታውም ሰፊም ስለሆነ በጣም የተሻለ እና በይበልጥ እንደቀሳቀሱ ምቹ መንገድ ለመንደሩ ይፈጥራል።
👉👉👉 በአብሮነት በመደመር በመልካም አስተሳሰብ አንድ በመሆን የተሸላች ውብ ምቹ ለምለም እና እንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ በር መክፈት እንችላለን።
👉👉ሪፎርም መሆኑዋ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም ለዛ እምሆን በጀት እስክሚመደብ መቆየት ትክክል ስለልሆነ ተነስተን በመስራት ከወድሁ ለመረጠውና ለውጥ ለሚፈልጉ ለዳሞት ዎይዴ ተወላጆች የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ብታሳዩ የሚል ሀሳብ አለኝ።።።።
።።።። ያገባኛል የምንል ሀሳባችሁን አስቀምጡ።።።።።
።።።።። እንዲሁም ሼር በማድረግ ለሚመለከተው እናድርስ ።።።።።
።።።።።።።ለውጥ እና ውበት ለወረዳችን።።።።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 via Abinet Teferi

Address

Bedessa
Bedessa

Telephone

+251978843190

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bedessaን በስልካቸን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category