ቢኒያም እንቻለው- Biniam Enchalew

ቢኒያም እንቻለው- Biniam Enchalew Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቢኒያም እንቻለው- Biniam Enchalew, debre markos, Bahir Dar.

03/09/2025

ነሐሴ 29 የበዓል ሁሉ ራስ የሆነው በዓለ ወልድ /በዓለ እግዚአብሔር ነው።
/አደረሰን!

Back to back ✅️
03/09/2025

Back to back ✅️

💚አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው❤️🌿❤️ ዘወትር እግዚአብሔ ከሁላችን ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን🌿🌿❤️ አማኑኤል ማለት  አማኑ ኤል፣  የአምላክ ሰላም፣ የእግ...
03/09/2025

💚አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው❤️
🌿❤️ ዘወትር እግዚአብሔ ከሁላችን ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን🌿

🌿❤️ አማኑኤል ማለት አማኑ ኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው።
« 🌿❤️ አማነ»እና «ኤል» ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛጋ ማለት ነው።

« 🌿❤️ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ»

🌿❤️ «ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡» ( ኢሳ 7፥14)

🌿❤️ ክብር ፣ኃይልና ምስጋና ለአምካችን ለአማኑኤል ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።
❤️💚❤️💙💖💜
❤️💚❤️💙💖💜💚💓❤️💖
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

የዲያቆን ጌቱ ተሾመ አስደናቂው ምላሽ !!!😳🤔 አንድም ሰው ይህቺን ልጅ በበቂ አመክንዮ ሲሞግታት ዐላየሁም። አንድም ሰው አልሞገታትም። እኔ በግሌ በግልጽ ስላነሣችው እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል...
02/09/2025

የዲያቆን ጌቱ ተሾመ አስደናቂው ምላሽ !!!😳🤔 አንድም ሰው ይህቺን ልጅ በበቂ አመክንዮ ሲሞግታት ዐላየሁም። አንድም ሰው አልሞገታትም። እኔ በግሌ በግልጽ ስላነሣችው እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። ጋብቻን እስካልነቀፉ፣ ብልግናን እስካላበረታቱ... ድረስ በድፍረት ወጥተው የኅብረተሰቡን ችግር ለማሳየት የሚጥሩትን አደንቃለሁ።

ስለ ልጅቷ ፐርሰናሊቲ አላወራም። አላውቃትም። ግን ማን ያዘዋልና እግረኛው ጋር ቀርባ ያወራቻቸው ትክክል ናቸው። ስንቱ ወጣት ይሄንን ተግባር አደባባይ ላይ ይፈፅማል። "ከትዳር ውጪ የሚደረግ ግንኙነት ዝሙት ነው" ብለን ብናምንም ስንቱ ይህንን እንደሚተገብር አናውቅም። ግለ ወሲብም ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ግንኙነትም ጸያፍ ነው። ይህንን በግልጽ አውጥተው "ከዚህ እንዴት እንውጣ?" የሚሉ ሰዎችን ማጥላላት አስቂኝ ነው። በድብቅ የሚተገብር ሰው በሞላበት ኹኔታ "ስለዚህ አይወራም፤ የሕዝቡን ዕሴት ይንዳል" አይባልም። ካስፈለገ ለምን እንክትክቱ አይወጣም። ስንት ወላጆች ልጆቻቸውን ከዚህ ሱስ ማውጣት ያልቻሉት በግልጽ ስለማያወሯቸው ብቻና ብቻ ነው።

ይህን ችግር ማስተካከል ያልቻልነው ፍትወት ተፈጥሮአዊ መኾኑን ማመን ስላልፈለግን ነው። ሰው የተባለ ኹሉ የወሲብ ፍላጎት አለው። አይደለም እኛ ቀርቶ ዕድሜ ልካቸውን ከተቃራኒ ጾታ ርቀው የሚኖሩ መነኰሳት የዚህ ፍላጎቱ አላቸው። የመቋቋምና ያለ መቋቋም እንጂ ፍላጎቱ በሰው ኹሉ ላይ ያለ ነው። አጉል ጨዋ ለመኾን ስንሞክር ይህንን ማመን አንፈልግም። ብዙዎች ወደ ግለ ወሲብ፣ ወደ ዝሙት የሚገቡት ይኼ የተፈጥሮ ፍላጎት በውስጣቸው ስላለ ነው። አስቀድመን ይህንን እውነታ እንረዳ።

ይህንን ፍላጎት ሥራ ላይ ማዋል እንደሚቻል አወራች። በቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ፍትወት ሲነሣ እንድንሠራ፣ እንድንሰግድ... የሚነገረን ለዚህኮ ነው። በፖርኖግራፊ፣ በማስተርቤት... ጉዳይ ወጣቱን የሚያሳትፉ ዝግጅቶች መደረግ አለባቸው። በሽታው የተደበቀ መድኃኒቱ አይገኝም።በርቺ ሲስቱካ !!!❤️🙏❤️

©ዲያቆን ጌቱ ተሾመ

02/09/2025

ዛሬ ቀኑ ማክሰኞ ነው
ያልገመታችሁት በረከት
ወደ ቤታችሁ ይግባ✅️🙏

02/09/2025

ማረኝ

ሊቨርፑል አርሰናልን 1 ለ 0 አሸነፈአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል አርሰናልን 1 ለ 0 አሸንፏል።ምሽት 12 ...
31/08/2025

ሊቨርፑል አርሰናልን 1 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል አርሰናልን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች መጠነኛ የጨዋታ እንቅስቃሴ አድርገው እስከ 80ኛው ደቂቃ ያለ ግብ ቆይተዋል።

ሆኖም የሊቨርፑሉ አማካይ ዶሚኒክ ስቦዝላይ በ83ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ድንቅ የቅጣት ምት ሊቨርፑልን አሸናፊ አድርጋለች።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ9 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን ሲመራ አርሰናል 6 ነጥቦችን በመያዝ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የ3ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ሲደረግ ምሽት 3 ሰዓት አስቶንቪላ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

31/08/2025

እናትነት �

ምን ተማራችሁ ?ማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ዩቲዩብ፣ ለታዳጊ ወጣቶች የትምህርትና የመዝናኛ ምንጭ ነው። ነገር ግን ገንዘብንና ዝናን ብቻ ታሳቢ ባደረጉ አንዳንድ የዩቲዩብ ቻናል ባለቤቶች አማካይ...
31/08/2025

ምን ተማራችሁ ?

ማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ዩቲዩብ፣ ለታዳጊ ወጣቶች የትምህርትና የመዝናኛ ምንጭ ነው።

ነገር ግን ገንዘብንና ዝናን ብቻ ታሳቢ ባደረጉ አንዳንድ የዩቲዩብ ቻናል ባለቤቶች አማካይነት የሚቀርብ መጥፎ መልዕክቶች አሳሳቢ ናቸው።

በዩቲዩብ ላይ የሚቀርቡት ይዘቶች የብዙ ታዳጊዎች አመለካከት እና ባህሪ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አላቸው።

ስለዚህም፣ ጠቃሚ እና አስተማሪ ይዘቶችን ከማቅረብ ይልቅ፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለህብረተሰቡ የማይጠቅሙ ነገሮችን የሚያስተላልፉ ቻናሎች ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

መንግስት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚተላለፉትን ጎጂ ይዘቶች የመቆጣጠር ሃላፊነት አለባቸው።

ለወጣቶች የተሻለ እና አስተማማኝ የመማሪያ መድረክ መፍጠር የሁላችንም ሃላፊነት ነው።

እናንተስ፣ አሁን ከዚች ልጅ ምን ተማራችሁ?

አስተያየታችሁን አካፍሉን።

😎😎😎

🌴🌴🌴

ምላ ሴkስ ታያለህ አትዋሽ ያለችው ፓርት ጋዜጠኛውን ኧረ ወገን አልቻሏትም ለ3 😂😂🤭
31/08/2025

ምላ ሴkስ ታያለህ አትዋሽ ያለችው ፓርት ጋዜጠኛውን ኧረ ወገን አልቻሏትም ለ3 😂😂🤭

✝አባቴ  #መድኃኔዓለም ሆይ በቸርነትህ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀን ✝🙏  #መድኃኔዓለም ሆይ ከሰው ወገን ማንም እንደእኔ ኃጢአትየሰራ  #በደለኛ እንደ አንተም  #ይቅር ባይ  #አምላክ የለም። ...
03/08/2025

✝አባቴ #መድኃኔዓለም ሆይ በቸርነትህ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀን ✝🙏

#መድኃኔዓለም ሆይ ከሰው ወገን ማንም እንደእኔ ኃጢአት
የሰራ #በደለኛ እንደ አንተም #ይቅር ባይ #አምላክ የለም።
! ዓለማትን ኹሉ የፈጠርኽ ነኽና በኋለኛው ዘመን በዓለም ላይ ለመፍርድ በምትመጣበት ጊዜ ከጎንህ በፈሰሰው #ደም ኃጢአቴን እጠብልኝ አሜን✝🙏



የጌታችንና የመድኃኔታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነቱ ይቅርታው ምህርቱ የአባትነት ፍቅሩ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ በእውነት ይደርብን አይለየን አሜን
በሃይማኖት ያፅናን በምግባር ያቅናን አሜን✝🙏💚💛❤

Address

Debre Markos
Bahir Dar
DENMARK

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቢኒያም እንቻለው- Biniam Enchalew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Museum

Send a message to ቢኒያም እንቻለው- Biniam Enchalew:

Share