ADWA VICTORY MEMORIAL OF ETHIOPIA

ADWA VICTORY MEMORIAL OF ETHIOPIA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ADWA VICTORY MEMORIAL OF ETHIOPIA, History Museum, Addis Ababa, Addis Ababa.

23/01/2025
Teeknooloojiin abjuu hirriiba keessa arginu akka fiilmiitti irra deebisee namatti agarsiisu ifoome.  Onkololeessa 18,201...
28/10/2024

Teeknooloojiin abjuu hirriiba keessa arginu akka fiilmiitti irra deebisee namatti agarsiisu ifoome.
Onkololeessa 18,2017- Qorattoonni Jaappaan meeshaa abjuu hirriiba keessa nama mudatan waraabuun irra deebiin bifa fiilmiin namatti agarsiisu ifoomsan.
Qorattoonni kunneen Artiifishaal Intalajansii AI fi teeknooloojii fakkii sammuu fudhachuu danda’an fayyadamuun kan abjuu galmeessuufi bifa fiilmiin namatti agarsisuu kalaquu ibsan.
Teeknooloojiin kun sosochii narviiwwanii abjuu waliin walqabatan galmeessuuf M.R.I ( Magnetic resonance imaging) fayyadama.
Kalaqni kun sosochii sammuu fayyadamuun humna haalota abjuu tokko tokkoo ibsuu qaba.
Yaalii teeknooloojii kanarratti godhameenis humni abjuu abjootan osoo hin jijjiiriin agarsiisuu harka 70 ol milki-qabeessa ta’uu marsariitiin News Eighten(18) jedhamu gabaaseera.
Teeknooloojiin kun fayyaa sammuu fooyyessuuf, miira namootaa ilaaluufi dhibeewwan xinsammuu waliin walqabatan qorachuuf hojiirra oolas jedhameera.

05/10/2024
 #ለ 55 ዓመታት በጓደኝነት የዘለቁት እና እድሚያቸው ከ 60 ዓመት በላይ የሚገመቱ ለራሳቸውም በጎዎቹ የሚል የጋራ ስያሜ የሰጡ 8 ሴት ጉዋደኛማቾች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ጉብኝት አ...
16/03/2024

#ለ 55 ዓመታት በጓደኝነት የዘለቁት እና እድሚያቸው ከ 60 ዓመት በላይ የሚገመቱ ለራሳቸውም በጎዎቹ የሚል የጋራ ስያሜ የሰጡ 8 ሴት ጉዋደኛማቾች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ጉብኝት አካሂደዋል።

መጋቢት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ከዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2016 ዓ.ም ለህዝብ እይታ ክፍት መደረጉን ተከትሎ ለ 55 ዓመታት በጓደኝነት የዘለቁት እና እድሚያቸው ከ 60 ዓመት በላይ የሚገመቱ ለራሳቸውም በጎዎቹ የሚል የጋራ ስያሜ የሰጡ 11 ሴት ጉዋደኛማቾች በመሃል ፒያሳ ቀጠሮ ይዘው በመታሰቢያ ሙዝየሙ ጉብኝት አካሂደዋል።

ከ 1 ኛ ክፍል አንስቶ አብረው መማራቸውን እና ወዳጅነታቸውም በሀዘን ይሁን በደስታ በማግኘት ይሁን በማጣት እንዳልተፈተነ የሚናገሩት ጉዋደኛማቾቹ በዛሬው እለት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየምን ለመጎብኘት ከያሉበት መሳበሰባቸውን ተናግረዋል፡፡

በጎ ተግባራትን ለመከወን ብቻ እንደሚገናኙ የተናገሩት እና እራሳቸውንም በጎዎቹ ብለው የሚጠሩት እነኚህ አዛውንት ሴቶች ከልጅነታችን ጀምሮ በትምህርት፣በሙዚቃ፣በቲያትር እና በመሰላሉት መንገዶች የምናውቀውን ዓድዋ ይህ የመታሰቢያ ሙዝየም የጦርነቱ አንድ አካል እንደሆንን እስኪሰማን ድረስ በምናብ ወስዶናል ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም ይህ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ግንባታው አልቆ ለህዝብ እይታ እንዲበቃ ላደረጉ አካላት በሙሉ “በጎዎቹ” ምስጋናን ቸረዋል፡፡

የዓድዋ ድል የተገኘው በኢትዮጵያውያን ፍቅር፣ ሕብርና ትብብር ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድልን ማሳካት የተቻ...
01/03/2024

የዓድዋ ድል የተገኘው በኢትዮጵያውያን ፍቅር፣ ሕብርና ትብብር ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድልን ማሳካት የተቻለው በህብር፣ ፍቅርና ትብብር ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

ዓድዋ ዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በዓድዋ የድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በዓድዋ ጦርነት በተባበረ ክንዳቸውና በአልገዛም ባይነት ወኔያቸው ወራሪ ኃይልን በማንበርከክ የሀገራቸውን ክብር አፅንተዋል።

የዓድዋ ድል በህብር፣ በፍቅርና በትብብር የተገኘ ግዙፍ ድል መሆኑን ጠቅሰው÷ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጦርም በህብረ ብሔራዊ አንድነት የተዋቀረ ሃይል መሆኑንም አንስተዋል።

የዓድዋ ዘማቾች ህብርነት የብሔር ብቻ ሳይሆን የመሪና የህዝብ፣ የከያንያንና የስንቅ አዘጋጆች፣ የሴቶች እንዲሁም ሁሉም ህብረት በመፍጠር ለሀገር ክብር የተመሙበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ዛሬም የኢትዮጵያን ጠላቶች ለማንበርከክ፣ ድህነትን ድል ለማድረግና ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለማሸነፍ ህብር ሆኖ መዝመት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በዓድዋ ዘመን የታየው የሀገርና የወገን ፍቅር ዛሬም ፀንቶ እንዲቀጥል መሥራት ይጠበቃል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ለሀገር የሚከፈል ዋጋ ከምንም በላይ ነው ብለዋል፡፡

ዓድዋ ሀገር የሚታደግና የሚያጸና ትምህርት ቤት በመሆኑ ስብራቶችን ለመጠገን ፍቱን መድሃኒት እንደሆነም አመላክተዋል።

በመሆኑም ከቀደምት ጀግኖች የሀገር ፍቅርን በመውረስ ለሀገር ሰላምና ብልፅግና እንዲሁም ለሀገረ መንግስት ግንባታ መትጋት የዚህ ዘመን ትውልድ ሃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

01/03/2024

ለነፃነት የተከፈለ የደም ዋጋ!
*******************

ሀገር እንድትቀጥል በተለያዩ ዘመናት ደም ፈሷል አጥንት ተከስክሷል ሕይወትም ተገብሯል። ሀገር በአንድ ጀንበር አትገነባምና በየዘመኑ ሁሉም የየራሱ የሽንፈት እና የድል ታሪክ አለው ።

ኢትዮጵያም በታሪኳ ብዙ ፈተናዎችን እየተሻገረች ድል እያደረገች በልጆቿ መስዋዕትነት የቆመች ሀገር ነች። የታሪክ ቀደምት ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ስትነሳ በዓለም ህዝብ ዘንድ በጉልህ ከሚታወሱ ታሪኮቿ ውስጥ የአፍሪካ የነፃነት ቀንዲል መሆኗ ተጠቃሽ ነው።

የምናወራው ስለመውደቅ ወድቆ ሰለመነሳትም አይደለም፤ ይልቁንስ አንገትን ቀና አድርጎ ደረትን ነፍቶ እኛ ማንም ያልደፈረን ነፃ ህዝቦች ነን ብሎ ስለመቆም እንጂ።

ይህ ታሪክ እንዲህ ነው የሚጀምረው የአውሮፓ ኃያላን መንግስታት በዓለም ላይ ከኛ ውጭ ፈላጭ ቆራጭ፣ ገዢም አዛዥም የለም በሚሉበት በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ ትልቅ ስብሰባ የጀርመኗ በርሊን ከተማ አስተናገደች።

እ.ኤ.አ 1884 የተከናወነው የበርሊን ስብሰባ ትልቁ አጀንዳና ምክንያት ደግሞ አውሮፓውያን አፍሪካን እንደምን እንደሚቀራመቷት ለመቀየስ ነበር። ንግግሩና ውይይቱ ያተኮረው እንደምን በሚለው ላይ ብቻ ነበር፤ ለምን? እንዴት ? የሰውን ሀገር መውረር ይቻላል የሚለው ጥያቄ ጉዳያቸው አልነበረም ምክንያቱ ደግሞ አፍሪካውያን የቆዳቸው ቀለም ጥቁር በመሆኑ።

አስገራሚው ነገር እነዚህ አውሮፓውያን አህጉሪቷን በሙሉ በቅኝ ግዛት መያዝ መፈፀም ያለበት እንጂ የሚያከራክር ጉዳይ አልነበረምና ውሳኔውን ለመወሰን ምንም አልያዛቸውም፤ በዚህም መሰረት አውሮፓውያኑ አፍሪካን ተቀራመቷት።

ፈረንሳይ 34 በመቶ፣ እንግሊዝ 32 በመቶ፣ ጀርመን 7 በመቶ፣ ቤልጄም 7 በመቶ፣ ስፔን 7 በመቶ፣ ፖርቹጋል 6 በመቶ፣ ጣሊያን 5 በመቶ እና ነፃ ሀገራት 2 በመቶ ድርሻን ያዙ ሲሉ ተድላ ዘዮሃንስ የኢትዮጵያ ታሪክና ጣሊያን በኢትዮጵያ በሚለው መጽሐፋቸው አስፍረውታል።

ይህ ሚዛን ነው እንግዲህ የጣሊያንን መንግስት ክብር የሚቀንስ ሆኖ በጣሊያን ባለስልጣናት ዘንድ የታየው። በዛን ጊዜ ጣልያን የያዘቻቸው የሊቢያ የሶማሊያና የኤርትራ ምድር አብዛኛው በርሃማ ሆነባት ስለዚህ ዓይኗን በኢትዮጵያ ላይ ጣለች።

ነገር ግን ጣልያን ጥሩ ገድ አልገጠማትም፤ ምክንያቱም የመጣችው አንነካም ከነኩንም አንለቅም፤ በሀገራችን አስተዳደር ብንከፋም እንኳን "ሀገራችን ሌላ አስተዳደር ሌላ" ብለው ክንዳቸውን ከፍ በሚያደርጉበት ኢትዮጵያውያን ቀዬ ነበር።

በሰው ልጆች እኩልነት የሚያምኑትና ፈጣሪ ፈቅዶ በሰጠን ሀገራችን ላይ ማንም ከውጭ መጥቶ ሊያዘን፣ ሊገፋን ጉልበታችንን ሊበዘብዝ፣ በቆዳችን ቀለም ሊያጣጥለን አይችልም፤ ያሉት የኢትዮጵያ አርበኞች የሚሳሱለትን ቤታቸውንና ቀያቸውን ወደ ኋላ ትተው ጋሻ እና ጦራቸውን ታጥቀው የንጉሳቸውን ጥሪ ተቀብለው ፋሽስትን ወደ መጣበት ለመመለስ በፈረስ በበቅሎ አለፍ ሲልም በእግራቸው ወደ ዓድዋ ተራሮች ገሰገሱ ።

ወረዱ ዓድዋ ላይ ጀግኖች ከየቤቱ
የልባቸው እሳት ተመዞ ካፎቱ
በዛ እንደብልጭታ መድፍና ጥይቱ
ዳናው በረከተ ፎከረ ካንጀቱ
የሰው የፈረሱ ጠፋው ምልክቱ
ታጥቆ ሰው ሊገዛ እጣው ቢደርስበት
ባመጣው መሳርያ ገናን ክንድ አርፎበት
የወደቀው ወድቆ ታሪክ ተፃፈበት

እንዳለው ዜመኛው ከእምዬ ኢትዮጵያ በፊት እኔን ያስቀድመኝ የሀገሬን ክፉ ከማይ ብሞት ይሻላል ባሉ ኢትዮጵያዊ ጀግና አርበኞች መስዋዕትነት እና በአፄ ሚኒሊክ፣ በእቴጌ ጣይቱ እንዲሁም በጦር መሪዎችና ራሶች አጋፋሪነት ጣሊያን በጥቁር ጀግኖች ድል ተመታች ።

ይህ የሆነው እንግዲህ ከዛሬ 128 ዓመታት በፊት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ነበር ። ይህ ድል ለድል አድራጊዎች ኢትዮጵያውያን፣ ለአፍሪካውያን እና ለመላው የጥቁር ህዝብ የአሸናፊነት መንፈስ ሲያጎናፅፍ፤ በአንፃሩ የጣሊያን ሽንፈት ነጮችን በጦርነት መርታት እንደሚቻል ለመላው የዓለም ህዝብ ያሳየ ክስተት ሆነ።

ድሉን ተከትሎም የኢትዮጵያን በነፃነት መኖር የወቅቱ ኃያላን ሀገራት እንግሊዝና ፈረንሳይ ግልፅ እውቅና እንዲሰጡ አደረጋቸው።

ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትም ጣሊያንን ጨምሮ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ሀገርነት ተራ በተራ ተቀበሉ ። የጣሊያን ተሰሚነት በጊዜው በዓለም ሀገራት ዘንድ ሲቀንስ የኢትዮጵያ ድልና ዝና በመላው ዓለም ናኘ።

ዛሬ አንገታችንን ቀና አድረገን እኛኮ የእነዛ ጀግና ልጆች ነን ብለን እንድንኮራ የሆነው ያኔ አባቶቻችን ከሰሜን ከደቡብ ከምዕራብና ከምስራቅ ተጠራርተው የቤታቸውን ችግር እና የአስተዳደርን ኩርፍያ ወደጎን ትተው በዓድዋ ተራሮች ግርጌ በከፈሉት መስዋዕትነት ነው።

ዛሬም ሀገር እንድትቀጥል የዘመናችን ፋሽስት ሆኖ ፊታችን ላይ የቆመውን ድህነትና ፅንፈኛ ብሔርተኝነት እንቢ ብለን በማስወገድ በአንድነት ሀገራችንን እንድንገነባና ዳግማዊ ዓድዋን በዚህ ዘመን እንድንፅፍ ይጠበቃል።

ምስጋና ትላንት በደማቸው ሀገርን አፅንተው ዛሬን ቀና ብለን እንድንሄድ ላደረጉን አባቶቻችን።

እንኳን ለ128ተኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

በናርዶስ አዳነ

The Battle of Adwa holds a special place in world history, extending its significance far beyond the borders of Ethiopia...
29/02/2024

The Battle of Adwa holds a special place in world history, extending its significance far beyond the borders of Ethiopia. Here's how Adwa's impact resonated on the global stage:

1. **Defiance of Colonial Powers**: Adwa marked a pivotal moment where an African army, under Emperor Menelik II, decisively defeated a European colonial power, Italy. This unprecedented victory challenged the prevailing notion of European military invincibility and sent shockwaves across the world.

2. **Inspiration for Anti-Colonial Movements**: The triumph at Adwa served as a beacon of hope and inspiration for anti-colonial movements worldwide. It showed that colonial powers could be resisted and defeated, igniting a sense of determination among colonized peoples in Africa, Asia, and beyond.

3. **Symbol of African Independence**: Adwa became an enduring symbol of African resistance and independence. It showcased Ethiopia's ability to maintain sovereignty in the face of aggressive colonial expansion, highlighting the strength and resilience of African nations.

4. **Shift in Global Power Dynamics**: The Battle of Adwa contributed to a shift in global power dynamics by challenging European imperialism. It demonstrated that African nations were capable of defending themselves, prompting changes in colonial policies and increasing international respect for African sovereignty.

5. **Promotion of Pan-Africanism**: Adwa played a significant role in promoting Pan-Africanism, the movement advocating for the unity and solidarity of African peoples worldwide. The victory emphasized the shared history and struggles of Africans against colonial oppression, fostering a sense of collective identity and purpose.

6. **Impact on World History**: Historically, Adwa is regarded as a watershed moment that influenced the trajectory of colonial history. It contributed to the decline of Italian imperial ambitions in East Africa and shaped how European powers approached their colonial ventures in the region.

23/02/2024

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ADWA VICTORY MEMORIAL OF ETHIOPIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category