14/09/2026
ሳምንቱ በዓድዋ ድል መታሰቢያ!
ባለፈው ሳምንት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሃገር አቀፍ መድረኮች፣ ባህላዊ ኩነቶች እንዲሁም የውይይት መድረኮች የተከናወኑበት ልዩ ሳምንት ነበር፡፡
የሳምንቱ ዋና ዋና ኩነቶች፦
• «የጽናት ቀን» በዓድዋ ድል መታሰቢያ፦ የአዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ «የጽናት ቀን» በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር እና በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ አዘጋጅነት በመታሰቢያው በድምቀት ተከብሯል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።
• ህብር የማርሻል አርት ፌስቲቫል፦ «የህብር ቀን»ን በማስመልከት «ህብር የማርሻል አርት ፌስቲቫል» በሚል መሪ ቃል ከ50 ሺህ በላይ የማርሻል አርት ቤተሰቦች የተሳተፉበት ታላቅ ፌስቲቫል በዓድዋ ፕላዛ ተካሂዷል። በዕለቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ፣ በዓሉ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በሚያጠናክሩ የጋራ እሴቶች ላይ በማተኮር መከበሩን ገልጸዋል።
• የህብር ቀን ባህላዊ ኩነቶች፦ ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን የሚያበስሩ ውብ እና ህብራዊ ባህሎቻችን የሆኑት የአበባአየሽ ወይ፣ የአሸንዳ፣ ጎቤ፣ ሽኖዬ እና ሻደይ ጭፈራዎች በታሪካዊው ዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተከብረዋል።
--------//////-----
This Week at the Adwa Victory Memorial!
Over the past week, the Adwa Victory Memorial hosted a series of notable national forums, cultural events, panel discussions, and graduation ceremonies.
Key Highlights of the Week:
• "Day of Resilience" Celebrated at the Memorial: As part of the Ethiopian New Year transition, the "Day of Resilience" was colorfully celebrated at the Memorial. The event was jointly organized by the FDRE Defense Forces, Ethiopian Federal Police, National Intelligence and Security Service, Information Network Security Administration, and the Ethiopian Artificial Intelligence Institute. High-ranking federal and regional officials, including FDRE House of Federation Speaker Honorable Agegnehu Teshager, alongside leadership and members of security agencies, were in attendance.
• Unity Martial Arts Festival: Marking "Unity Day," the grand "Unity Martial Arts Festival" took place at Adwa Plaza, gathering over 50,000 martial arts enthusiasts. Speaking at the event, Deputy Head of the Addis Ababa City Communication Bureau, Mr. Zewdu Kebede, highlighted that the celebration focused on shared national values that reinforce multinational unity.
• Unity Day Cultural Events: Celebrating the transition into the New Year, vibrant traditional performances, including Abeba Ayesh Wey, Ashenda, Gobe, Shinoye, and Shadey, were colorfully showcased at the historic Adwa Victory Memorial.
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication Mayor Office of Addis Ababa Addis Ababa Education Bureau
የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይጎበኙ!
Facebook: https://web.facebook.com/adwavictorymemorial
TikTok : - https://www.tiktok.com/
LinkedIn https://www.linkedin.com/.../adwa-victory-memorialethiopia
Telegram: https://t.me/adwa_victory_memorial_gov_et
Instagram : https://www.instagram.com/adwavictorymemorial_official