28/02/2026
ሰባ ስምንት ዓመቴን ጨርሼ 79ነኛውን ጀመርኩት፡፡ ሰባ ስምንት ሞላኝ እንደሚሉት፡፡ ትላንት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የዳበረውን፡ የታረመውን፡ የተማርኩበትን Emperor Menelik II: A Panafrican Military Strategist and Diplomat በሚል ርዕስ የታተመውን ለደራሲው በነጻ የሚሰጡ አሥር ኮፒዎችን አስረከበኝ፡፡ እንደ አጋጣሚ እንኳን ለ78ኛው ዓመትህ አደረሰህ እንዳለኝ ቆጠርኩት፡፡ ቀደም ሲል የበረውን Emperor Menelik II: The Military Strategist and Diplomat Who Changed the Course of History በሚል ርዕስ ከታተመው በጥልቀቱ ምን ያህል እንደሚበልጥ ስታነቡት ትረዱታላችሁ፡፡