13/02/2024
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡
ጉበኝቱ ከዛሬ ጀምሮ በተቀመጠው መርሃግብር መሰረት ለጎብኒዎች ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
በተቀመጠዉ መርሀ ግብር መሰረት በዛሬዉ እለት የክፍለ ከተማ ና ወረዳ አመራሮች የአድዋ ድል መታሰቢያ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተደሳደር በስሩ ከሚገኙ አራቱ ክፍለ ከተሞች ማለትም አዲስ ከተማ፤ጉለሌ፤የኮልፌና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አመራሮች የአድዋ ድል መታሰቢያ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑት የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች የአድዋ ድል የኢትዮጵያና የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌት እና ነፃነት አርማ እንዲሆን ያስቻለንን ይህ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ለ128 ዓመታት ታሪኩን በሚመጥን መልኩ በአንድነት ሳናከብረዉ ብንቆይም አሁን ግን ታሪካችንን ከመስማት በዘለለ በእዉን እንድናይና እንድንረዳ ያስቻለን የአድዋ ድል መታሰቢያ ነዉብለዋል፡፡
አክለዉም እኛም ሆነ ቀጣዩ ትዉልድ ልክ እንደ ጀግኖቻችን የሀገር ፍቅርን፤ፅናትን፤አይበገሬነትን፤ መደጋገፍንና አንድነትን ወርሰን ለሀገራችን ሰላም፤ልማትና ብልፅግና ሁላችንም የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ይሄን የሰሩ እጆች ይባረኩ ብለዋል::