Amba Hawaz

Amba Hawaz አምባ ሐዋዝ የበገና አምባ ሲሆን ከበገና ጋር ተያያዥ የሆኑ ምርት እና አገልግሎቶችን ይሰጣል።

በገና የድምፆች ዙፋን ነው፨፣ደውለው ይዘዙን+251 980332101+251 965186617ወዳሉበት ሁሉ እንልካለን። #በገና
16/05/2026

በገና የድምፆች ዙፋን ነው፨



ደውለው ይዘዙን

+251 980332101
+251 965186617

ወዳሉበት ሁሉ እንልካለን።

#በገና

10/05/2026

አሊ ሲሞት መብሌ ጉበት ምን ማለት ሊሆን ይችላል?

በገናን ለመማር ያሰቡ እንደሆን በዚህ ይደውሉልን
+251 980332101

ብሥራተ ገብርኤል በአዶት በኩል ገባ እንዳሉ ክላሲክ ዴንታል ያለበት ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ያገኙናል።

#በገና #ታሪክ #አምባ

09/05/2026

ስለ 'ይበላሃላ' ምን ያህል ያውቃሉ?

#በገና #ታሪክ #አምባ

መጋቤ ኅሩያን ቀሲስ መፅናኛዬ ከቤተሰባቸው ጋር በመዘክራችን ያደረጉት ጉብኝት እና ቡራኬ በከፊል።Yesterday our museum recieved a blessing from the visit of ...
02/05/2026

መጋቤ ኅሩያን ቀሲስ መፅናኛዬ ከቤተሰባቸው ጋር በመዘክራችን ያደረጉት ጉብኝት እና ቡራኬ በከፊል።

Yesterday our museum recieved a blessing from the visit of Megabe Hiruyan Qesis Metsenagnaye and his family.

#በገና

አምባ ሐዋዝ የበገና ቤተ መዘክር እና ትምህርት ቤት  ተመርቆ ተከፈተ!ሚያዚያ 8፣ 2018ክርስቶስ ተንሥኣ እሙታንበአቢይ ኃይል ወሥልጣንአሰሮ ለሰይጣንአግአዞ ለአዳምሰላምእምይእዜሰኮነፍስሐ ወሰ...
16/04/2026

አምባ ሐዋዝ የበገና ቤተ መዘክር እና ትምህርት ቤት ተመርቆ ተከፈተ!

ሚያዚያ 8፣ 2018

ክርስቶስ ተንሥኣ እሙታን

በአቢይ ኃይል ወሥልጣን

አሰሮ ለሰይጣን

አግአዞ ለአዳም

ሰላም

እምይእዜሰ

ኮነ

ፍስሐ ወሰላም

አምባ ሐዋዝ የበገና ቤተ መዘክር እና ትምህርት ቤት ተመርቆ ተከፈተ። ያለፈውን አሁን ያለውን እና ወደፊት የሚመጣውን በገነኛ ትውልድ ለማስተሳሠር ታልሞ የተሰናደው ይህ አምባ የተከፈተው ሚያዚያ 6 በቅዱስ ዳዊት ዓመታዊ በዓለ ልደት ላይ ነበር። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ታላላቅ በገና ደርዳርያን እና መምህራን፣ ሰባኪያነ ወንጌል፣  ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እንግዶች እና የበገና ወዳጆች የተገኙ ሲሆን ቀሲስ ብሥራት ሐለፎም መርሐግብሩን በጸሎት እና በቡራኬ አስጀምረውታል። 

በመቀጠልም ተጋባዥ እንግዶች መዘክሩን በጎበኙበት ወቅት ስለስብስቡ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በዚህ መዘክር ውስጥ ቅዱስ ዳዊት በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን ሠዓልያን ውስጥ የነበረውን መልክ የሚያስቃኘው ትዕይንት የመጀመርያው ሲሆን፣ እምብዛም የሚታወቁት እናት በገነኞችን የሚያስቃኘው ትዕይንት ደግሞ ሁለተኛው ነው።  የመጨረሻው እና ሠፊው ትዕይንት ደግሞ በ1900ዎቹ ውስጥ የነበሩ በገነኞችን ታሪክ በከፊል የሚያሳየው ትዕይንት ነው። 

በማስከተል በመካሻ መኮንን እና እሌኒ ፋሲል የበገና ዝማሬ የቀረበ ሲሆን  ስለ አምባው አመሠራረት እና ጉዞ በአምባው ሥራ አስኪያጅ ምንተስኖት ተስፋዬ መግለጫ ተሰጥቷል።

በትውልድ ቅብብሎሽ የመጡ ነገሮችን ጠብቆ ማስጠበቅ የሁላችንም ታሪካዊና መንፈሳዊ ግዴታ ነው ያሉት ሊቀ ልሳናት መምህር ሲሳይ ደምሴ ሁሉ የሚሰምረው በንስሐ ሕይወት እና በቅዱስ ቁርባን ሲታጀብ እንደሆነ አጽኖት ሰጥተው መልዕክት አስተላልፈዋል። መርሐግብሩ ላይ በመገኘታቸው እና የተጀመረውን ሥራ በማየታቸውም እንደተደሰቱም ገልጠው ወደፊት ብዙ ሥራ እንደሚያስፈልግ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

በገናን በሚመለከት ይህን የመሰለ ስብስብ አምጥቶ ማሳየት እና ለዚህ መብቃት ትልቅ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ የበገና ትውፊት በነበረበት ሁኔታ መቀጠል አለበት እንጂ መለወጥ የለበትም የሚል ታላቅ አደራንም ሰጥተው አባታችን የተሰኘውን ተወዳጅ ዝማሬአቸውን አሰምተዋል።

አምባ ሐዋዝ የፊታችን ሰኞ ሚያዚያ 12 ትምህርት መስጠት በይፋ የሚጀምር እንደመሆኑ ለምዝገባ ክፍት መደረጉም ተገልጿል።

በመጨረሻም መርሐግብሩን በቡራኬ ያስጀመሩት ቀሲስ ብሥራት ሐለፎም ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን ማወቅን ማስቀደም እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ መርሐግብሩን በጸሎት ዘግተው አሰናብተዋል።

አምባ ሐዋዝ

ሚያዚያ 8፣ 2018 ዓ.ም

12/04/2026

ሰላምታ! እንኳን አደረሳችሁ!

አድራሻ: ብሥራተ ገብርኤል በአዶት በኩል ገባ እንዳሉ ክላሲክ ዴንታል ክሊኒክ ያለበት ሕንጻ 2ተኛ ፎቅ።



#በገና

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የሆሳዕና በዓል እና ሰሙነ ሕማማት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!።።በሚያዚያ 6 ከአምባው ታላቅ የምሥራች ይሰማል!
05/04/2026

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የሆሳዕና በዓል እና ሰሙነ ሕማማት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!



በሚያዚያ 6 ከአምባው ታላቅ የምሥራች ይሰማል!

03/03/2026

የአርበኛው ባለ በገና 2 ቅኝት

Arbegnaw Bale Begena event recap.

'አርበኛው ባለ በገና 2' ባሳለፍነው የካቲት ፳፩፣ ፳፻፲፰ ዓ.ም በልዩ ቅኝት ተካሄደ!አምባ ሐዋዝ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው 'አርበኛው ባለ በገና ' የቀደሙ አባቶቻችንን በተለያዩ ዝግጅቶች ዘ...
02/03/2026

'አርበኛው ባለ በገና 2' ባሳለፍነው የካቲት ፳፩፣ ፳፻፲፰ ዓ.ም በልዩ ቅኝት ተካሄደ!

አምባ ሐዋዝ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው 'አርበኛው ባለ በገና ' የቀደሙ አባቶቻችንን በተለያዩ ዝግጅቶች ዘክሯል።

መክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ክቡር ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ለበገና ያላቸውን ልዩ ፍቅር '....ውስጤን ያነጻዋል' ሲሉ ገልጠውታል ፤ በሁለተኛው የኢትዮጵያና ጣልያን ጦርነት ዘመን ታላቅ ተጋድሎ የፈጸሙት አባታቸው ራስ መስፍን ስለሺ በገናን አብዝተው ይደረድሩ እንደነበር እና ትውልዱም ይህንን የአባቶቹን ፈለግ መከተልና የተረሱ አባቶችን ይበልጥ ማስታወስ እንዳለበት በንግግራቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

በመቀጠል በወጣት በገነኞች አርበኛው ባለበገናን የሚያወሱ ዝማሬዎችን ጨምሮ ፤ በገና ደርዳሪዎች አድዋ ላይ የነበራቸው ሚና ለአሁኑ ትውልድ ያለውን ትርጉም ያሳየ ረቂቅ ተውኔት ለዕይታ ቀርቧል።

አስከትሎም በወቅቱ በጦርነት ላይ ተሳትፈው የነበሩ በገነኛ አባቶች ማንነት እና አበርክትዎ የሚያስቃኝ ወግ የቀረበ ሲሆን አምባ ሐዋዝ  እየሰራበት ያለውና ወደፊት በከፍታ ሊያስኬደው ያቀደውን የ"አኻያ" ንቅናቄ ለታዳምያኑ ይፋ ተደርጓል።

አርበኞችን የሚያወሱ ምስሎችና ቅርሶች ይዞ በልዩ አቀራረብ የተሰናዳው አነስተኛ መዘክር(Mini Museum) ሌላው የምሽቱ ገጽታ ሆኖ አልፏል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርን ጨምሮ ለመርሐግብሩ መሳካት ልዩ ልዩ አስተዋጽኦ ያደረጉትን አካላት አምባው ምስጋናውን አቅርቧል።

የካቲት 23፣ 2018 ዓ.ም
አምባ ሐዋዝ

21/02/2026

አርበኛው ባለ በገና 2፨

ለሀገር መስዋእት ሆነው ሀገርን ካቆሙ አርበኞች መካከል በገናቸውን አንግበው የዘመቱ ባለ በገናዎች ቁጥራቸው ሠፊ ነው። በታላቁ የአድዋ ጦርነትም ሆነ በሌሎች ሀገራዊ ውጊያዎች የበገነኞች ሚና ቀላል የሚባልም አልነበረም። አርበኛውን ባለ በገና በዝማሬ እና በተለያዩ ዝግጅቶች ስንዘክር በተጋድሎ የተረከብነውን ሀገር፣ እምነት እና ማንነት አስጠብቀን ጎዳናችንን እንድናቀና በማሰብ ነው።

ቀን እና ሰዓት: የካቲት 21/06/2018 ከ10:30 ጀምሮ

ቦታ: ከአብርሆት ቤ/መጻሕፍት ዝቅ ብሎ፣ ጠቅላይ ፍ/ቤት አጠገብ ባለው ቅያስ ገባ እንዳሉ በአዲሱ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ጽሕፈት ቤት 2ኛ ፎቅ (በተመዘገቡበት ቁጥር location ይደርስዎታል)

መግቢያ: በነጻ

Bio ላይ ባለው መመዝገቢያ መመዝገብዎን እንዳይረሱ፨
(RSVP mandatory)

ለበለጠ መረጃ
+251 980332101
+251 965186617
ይደውሉ፨

አምባ ሐዋዝ፨

#አድዋ #በገና

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amba Hawaz posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share